image
image
image
image
image

የመንግስት ሰራተኞች የሙያ ስነ-ምግባርን አክብረው በመስራት ሙስናን የመከላከል ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ

ህዳር 15, 2017
የልደታ ክ/ከተማ የመንግስት ሰራተኞች "ትውልድን በስነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር " በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለውን የፀረ-ሙስና ቀን በፓናል ውይይት አክብረዋል። የፓናል ውይይቱን የመሩት የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አሰፋ ቶላ እንደተናገሩት ነገን የተሻለ ለማድረግ ከሙስና የፀዳች ሀገር መገንባት ያስፈልጋል ብለው በዚህም ሙስናን በመከላከል ሂደት ሁሉም ባለቤት ሊሆንና ትግሉን ሊያቀጣጥል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ሙስና የስነ-ምግባር ዝቅጠት የሆነ የዜጎችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት በእጅጉ የሚጎዳ ተግባር ነው ያሉት አቶ አሰፋ ይህንን አስከፊ በሽታ መንቀል የምንችለው ሁላችንም በባለቤትነት በጋራ መዝመት ስንችል ነው በማለት ገልፀዋል። የመንግስት ሰራተኛው ሙስናን በመከላከል ተግባር ላይ የመሪነት ሚናውን ሊወጣ ይገባል ያሉት አቶ አሰፋ መንግስትም ተቋማትን እና አሰራራቸውን ለብልሹ አሰራር እንዳይመቹ ለማድረግ በየጊዜው ሪፎርም እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። መንግስት ሙስናን መከላከል የሚቻለው በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ መገንባት ሲቻል መሆኑን በመረዳት በትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አቶ አሰፋ ገልፀዋል። የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጄ በበኩላቸው ሙስናን መከላከል የምንችለው ጠንካራ ተቋም ስንገነባ ነው ብለው በዚህም መንግስት ተቋም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል። የልደታ ክ/ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ እንደተናገሩት ተቋማዊ አሰራርን በየጊዜው በመፈተሽና አገልግሎት አሰጣጣችንን በማዘመን ሙስናን የመከላከል ስራ እየሰራን ነው ብለው የመንግስት ሰራተኞችም የሙያ ስነ-ምግባራቸውን አክብረው በመስራት ሙስናን የመከላከል ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ጢቂ አክለውም የመንግስት ሰራተኞች ታማኝ በመሆንና ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት መንግስት ሙስናን ለመከላከል እየሰራው ያለውን ተግባር ሊያግዙ ይገባል ብለው ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ከሙስና እራሱን ነፃ አድርጎ ወደ ተግባሩ የሚገቡትን አምርሮ በመታገል ለውጥ እንዲመጣ መስራት አለበት በማለት ተናግረዋል። አስተዳደሩ ከተቋማት ሪፎርም በተጨማሪ አገልግሎት በቴክኖሎጅ እንዲደገፍ በማድረግ ከእጅ ንክኪ የፀዳ አገልግሎት እንዲሰጥ እየሰራ ነው ያሉት አቶ ጢቂ በዚህም ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራ እየሰራ ሲሉ ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው አስተዳደሩ ለልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለው የበለጠ ልማት እንዲሳለጥ የልማት ጎታች የሆነውን ሙስናን ለመከላከል በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች