image
image
image
image
image

ወጣቶች ሀገር በቀል የሠላም እሴቶችን በማጎልበት ሰላምና አብሮነትን ሊያጠናክሩ ይገባል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ

ጥቅምት 26, 2017
አስተዳደሩ "ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ" በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን ወጣቶች ሀገር በቀል የሠላም እሴቶችን በማጎልበት ሰላምና አብሮነትን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል። የክ/ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊና የዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ጢቂ ድሪባ በመድረኩ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት ሀገር በቀል የሠላምና የመቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለው ወጣቶች እነዚህን እሴቶች በማጠናከር አንድነትን፣ አብሮነትን እና መቻቻልን ሊያጠናክሩ ይገባል በማለት ገልፀዋል። መድረኩ ወጣቶች ሀገር በቀል የሠላምና የመቻቻል እሴቶችን ጠብቀው ለትውልድ በማሸጋገር ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን የክ/ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቶሎሳ መርጋ ተናግረዋል፡፡ አቶ ቶሎሳ አክለውም ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ወጣቶች ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ብለው ወጣቱ ለሰላም ለአብሮነትና ለአንድነት በጋራ መቆሙን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል በማለት ገልፀዋል። የክፍለ ከተማው የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት ሳሙኤል ዋለልኝ ፣በበኩላቸው ወጣቱ ችግሮች ሲያጋጥሙ በውይይት የመፈታት ባህልን የማዳበር ልምድ ሊያካብቱ ይገባል ብለው ወጣቶች በሰላም ግንባታ ላይ የደርሻቸውን እንዲወጡ ለማሰቻል እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች እንደገለጹት መድረኩ ችግሮች ሲያጋጥሙ በውይይት የመፍታት ባህልን እንድናዳብር እና ሀገር በቀል የሠላምና የመቻቻል እሴቶችን ጠብቀን ለትውልድ ለማሻገር ከፍተኛ አስተዋፆ አለው ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች