image
image
image
image
image

አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የተገልጋዩን ዕርካታ ማሳደግ እንደሚቻል የልደታ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ገለጸ።

ጥር 14, 2017
ጽ/ቤቱ የመጀመሪያውን 6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ከፈጻሚ፣ከአመራርና ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል ። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ተወካይ እና የፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደር እና ፋይናንስ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ እየሩሳሌም ዮሴፍ እንደገለጹት በጽ/ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ በማቀድና ከተለያዩ ጽ/ቤቶች ጋር የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ወደ ስራ መገባቱን ገልጸው ዕቅድን መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራዎችን መስራት ተችሏል ብለዋል። ወ/ሮ እየሩሳሌም አክለውም አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ፣ የለውጥ ስራዎችን አጠናክሮ በመስራት ፣ ስነ-ምግባር ያለው ሰራተኛ በመፍጠር ፣ ተቋማትን በመደገፍ ፣የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የተገልጋዩን ዕርካታ መጨመር መቻሉን ገልፀዋል ። የጽ/ቤቱ የሰው ሀብት ልማትና ስራዎች አስተዳደር ቡድን አስተባባሪ አቶ አዲስ ደጀኔ ከክ/ከተማውና ከወረዳ ተቋማት ጋር በጋራ ትክክለኛ መረጃዎችን በመለዋወጥና የሰው ሀይልን በመጠቀም የመንግስት ሰራተኛው በአገልጋይነት መንፈስ ተገቢውን አገልግሎት መስጠትና የጽ/ቤቱን ተግባራት በስታንዳርድ በማነፃፀር ስራዎችን መስራት አለበት ብለዋል። የጽ/ቤቱ በታቀደው ልክ ስራዎችን መስራት መቻሉን ጠቁመው በቀጣይም ጽ/ቤቱ የለውጥ ስራዎችን በትኩረት በመስራትና ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት ስራዎችን ቀጣይ በትኩረት መስራት የሚገባቸው መሆኑን ገልፀዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም የቀረበው የስድስት ወር አፈፃፀም ጥሩ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም በቅንጅት ውጤታማ ስራዎችን እንሰራለን ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች