image
image
image
image
image

በላቀ የአመራር ሰጪነት ከስኬታማ ባለሙያ ጋር ተግባራትን በቅንጅት በመስራት ተስፋ ሰጪ ለውጦች እየመጡ መሆኑ ተገለፀ

ጥቅምት 18, 2017
በመድረኩ የክ/ከተማው ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ ከክፍለ ከተማ እና ወረዳዎች ከተወጣጡ ዳሪክተሮች፣የስራ አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች ጋር በአገልግሎት አሰጣጥና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። የውይይት መድረኩን የመሩት የልደታ ክፍለ ከተማ ም/ ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አራርሳ ዲሪባ እንደገለፁት የልደታን ከፍታ ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዳሪክተሮች፣የስራ አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች የላቀ ሚና እንዳላቸው አንስተው በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚታዩ መሻሻሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በልዩ ቅንጅት እና መረባረብ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሩን ለመፍታት ለሰራተኛው ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አኳያ ስኬታማ ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ አራርሳ ድሪባ በ2018 ልደታን በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል። የውይይት መነሻ ሰነድ እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ያቀረቡት የልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጢቂ ዲሪባ እንደገለፁት በክፍለ ከተማው የአገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማነት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባው ገልፀው የውይይት መድረኩ ለስራዎች ስኬታማነት ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለፁት አስተዳደሩ ክፍለ ከተማውን ውጤታማ ለማድረግ አስተባባሪዎች እና ሰራተኞች የላቀ ሚና እንዳላቸው በማመን በቅርበት አብሮ እየተሰራበት ያለውን አግባብ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች