image
image
image
image
image

"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄዱ።

ሀምሌ 7, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤትና የወረዳ 8 አስተዳደር በጋራ አመራሮችንና የመንግስት ሰራተኞችን በማስተባበር 7ኛዉ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ችግኝ ተከላ አድርገዋል። የችግኝ ተከላውን ያስጀመሩት ያስጀመሩት የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሰፋ ቶላ ዓላማችን ዛሬ ላይ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ዛሬ የምንተክለው ነገ ለአገራችን ብሎም ለከተማችን የአየር ፀባይን ለማስተካከልና ጤናማና ለጤና ተስማሚ አየር እንዲኖረን በተለያየ አግባብ አገልግሎት ሊሰጡን የሚችሉ ችግኞችን በመትከል እንክብካቤ እና ክትትል በማድረግ ነገን በመንከባከብ ልናስቀጥል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። አረንጓዴ አሻራ የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ አጀንዳ ነው ያሉት አቶ አሰፋ ቶላ አያይዘው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ስናከናውን በላቀ ተነሳሽነት፣ ቁርጠኝነት ለሌላው አርአያነት በመሆን መትከልና በመንከባከብ እንደሚገባ ገልፀዋል ፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ እንደተናገሩት ባለሙያው አገራዊ ተልዕኮ ላይ የራሱን አሻራ ማሳረፍ መቻሉን በመግለፅ በየዓመቱ በሚደረገው የችግኝ መርሃ ግብር ላይ አላማውን በመረዳት የተቋሙ ባለሙያዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ ዛሬም አሻራቸውን በማሳረፍ እንደ አገር የተያዘውን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ሀላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪቃል እየተከናወነ በሚገኘው 7ኛው ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር ሰራተኞች በጊዶ ዋሻ በተዘጋጀው የችግኝ መትከያ ስፍራ በመትከል የዜግነት ድርሻችሁን ልትወጡ ይገባል በማለት ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች