የልደታ አስተዳደር ህንጻ 6ኛ ወለል
+251118549979
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
ተቋማዊ አደረጃጀት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
ደንብና መመሪያዎች
ማስታወቂያ
የደንበኞች አገልግሎት
የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች
አገልግሎቶች
ዲዛይን እና ግንባታ ፑል
ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፑል
ፐብሊክ ፑል
ለመልካም አስተዳደር አስተያየት
ለማንኛዉም ቅሬታዎ
የአገልግሎት እርካታ አስተያየት መስጫ
ለማንኛዉም ጥያቄዎ
የጽ/ቤቱን ሮቦት ይጠይቁ
አቅም ግንባታ
ሚዲያ
ዜና | News
Online TV
መጽሄቶች | Magazines
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ይግቡ
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
መጽሄቶች | Magazine
Online TV
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Web APP
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ይግቡ
ዜና | Oduu | News
የመንግስት ሰራተኞች የሙያ ስነ-ምግባርን አክብረው በመስራት ሙስናን የመከላከል ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ
ህዳር 15, 2018
የልደታ ክ/ከተማ የመንግስት ሰራተኞች "ትውልድን በስነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር " በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለውን የፀረ-ሙስና ቀን በፓናል ውይይት አክብረዋል። የፓናል ውይይቱን የመሩት የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አሰፋ ቶላ እንደተናገሩት ነገን የተሻለ ለማድረግ ከሙስና የፀዳች ሀገር መገንባት ያስፈልጋል ብለው በዚህም ሙስናን በመከላከል ሂደት ሁሉም ባለቤት ሊሆንና ትግሉን ሊያቀጣጥል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ሙስና የስነ-ምግባር ዝቅጠት የሆነ የዜጎችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት በእጅጉ የሚጎዳ ተግባር ነው ያሉት አቶ አሰፋ ይህንን አስከፊ በሽታ መንቀል የምንችለው ሁላችንም በባለቤትነት በጋራ መዝመት ስንችል ነው በማለት ገልፀዋል። የመንግስት ሰራተኛው ሙስናን በመከላከል ተግባር ላይ የመሪነት ሚናውን ሊወጣ ይገባል ያሉት አቶ አሰፋ መንግስትም ተቋማትን እና አሰራራቸውን ለብልሹ አሰራር እንዳይመቹ ለማድረግ በየጊዜው ሪፎርም እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። መንግስት ሙስናን መከላከል የሚቻለው በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ መገንባት ሲቻል መሆኑን በመረዳት በትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አቶ አሰፋ ገልፀዋል። የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጄ በበኩላቸው ሙስናን መከላከል የምንችለው ጠንካራ ተቋም ስንገነባ ነው ብለው በዚህም መንግስት ተቋም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል። የልደታ ክ/ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ እንደተናገሩት ተቋማዊ አሰራርን በየጊዜው በመፈተሽና አገልግሎት አሰጣጣችንን በማዘመን ሙስናን የመከላከል ስራ እየሰራን ነው ብለው የመንግስት ሰራተኞችም የሙያ ስነ-ምግባራቸውን አክብረው በመስራት ሙስናን የመከላከል ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ጢቂ አክለውም የመንግስት ሰራተኞች ታማኝ በመሆንና ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት መንግስት ሙስናን ለመከላከል እየሰራው ያለውን ተግባር ሊያግዙ ይገባል ብለው ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ከሙስና እራሱን ነፃ አድርጎ ወደ ተግባሩ የሚገቡትን አምርሮ በመታገል ለውጥ እንዲመጣ መስራት አለበት በማለት ተናግረዋል። አስተዳደሩ ከተቋማት ሪፎርም በተጨማሪ አገልግሎት በቴክኖሎጅ እንዲደገፍ በማድረግ ከእጅ ንክኪ የፀዳ አገልግሎት እንዲሰጥ እየሰራ ነው ያሉት አቶ ጢቂ በዚህም ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራ እየሰራ ሲሉ ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው አስተዳደሩ ለልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለው የበለጠ ልማት እንዲሳለጥ የልማት ጎታች የሆነውን ሙስናን ለመከላከል በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ አገልግሎት አሰጣጡን የሚያሳልጡ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ እና የስልጠና ማዕከል ፣የመሰብሰቢያ አዳራሾች ስታንዳርዳቸውን በጠበቀ መልኩ ስራ ጀመሩ
ህዳር 8, 2018
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጡን የሚያሳልጥ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከልን በዛሬው ዕለት ስራ አስጀምሯል። በሌላ በኩል የአመራሩንና የሰራተኞችን የመፈፀም አቅም ለማሳደግ የሚያስችል ራሱን የቻለ የስልጠና ማዕከልም በማዘጋጀት ስራ አስጀምሯል።
ዜና | Oduu | News
"ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር እና የሰራተኛውን እውቀት በአግባቡ በመጠቀም የተያዙ የልማት ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ ነው።"- ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ
ህዳር 8, 2018
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ለሰራተኛውና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የሚያስችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ስራ አስጀመረ። በዚህ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ አጠቃላይ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ዘላቂ እና ጠንካራ ተቋም ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለው ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር እና የሰራተኛውን እውቀት በአግባቡ በመጠቀም የተያዙ የልማት ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። አስተዳደሩ፤ በላቀ ትጋትና ቁርጠኝነት ህዝብን በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ልዕልቲ ሰራተኞች ደግሞ በታማኝነትና በቅንነት ህዝቡን እንዲያገለግሉ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል። የመንግስት ሰራተኞችን የኑሮ ጫናን ለማቃለል በመንግስት በኩል የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በስራው አከባቢ ያለአንዳች እንግልት አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችሉ ሰራተኛው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በቅረብ እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል። በዚህ መርሀ ግብር ላይ የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ለማሳለጥ የሚያስችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ ቴክኖሎጅዎችን ስራ ማስጀመሩን ወ/ሮ ልእልቲ አያይዘው ገልፀዋል። በዛሬው ዕለት ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት ማዕከል፣ ሱፐር ማርኬት፣ የህፃናት መጫዎቻ ስፍራ፣ የመጀመሪያ ህክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከል፣ ቤተ-መጽሃፍት እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ስራ አስጀምሯል። በተያያዘ አስተዳደሩ ስታንዳርዱን የጠበቀ የወረፋ ማስጠበቂያ፣ የውስጥና የውጭ ካሜራ መቆጣጠሪያ ሴንተር፣ ዲስፕሌዮች፣ ዲጅታል ዙም ሚቲንግ፣ QR ኮድ ያለው የሰራተኞች ባጅና ሌሎችንም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ተግባር አስገብቷል።
ዜና | Oduu | News
ወጣቶች ሀገር በቀል የሠላም እሴቶችን በማጎልበት ሰላምና አብሮነትን ሊያጠናክሩ ይገባል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ
ጥቅምት 26, 2018
አስተዳደሩ "ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ" በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን ወጣቶች ሀገር በቀል የሠላም እሴቶችን በማጎልበት ሰላምና አብሮነትን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል። የክ/ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊና የዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ጢቂ ድሪባ በመድረኩ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት ሀገር በቀል የሠላምና የመቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለው ወጣቶች እነዚህን እሴቶች በማጠናከር አንድነትን፣ አብሮነትን እና መቻቻልን ሊያጠናክሩ ይገባል በማለት ገልፀዋል። መድረኩ ወጣቶች ሀገር በቀል የሠላምና የመቻቻል እሴቶችን ጠብቀው ለትውልድ በማሸጋገር ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን የክ/ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቶሎሳ መርጋ ተናግረዋል፡፡ አቶ ቶሎሳ አክለውም ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ወጣቶች ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ብለው ወጣቱ ለሰላም ለአብሮነትና ለአንድነት በጋራ መቆሙን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል በማለት ገልፀዋል። የክፍለ ከተማው የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት ሳሙኤል ዋለልኝ ፣በበኩላቸው ወጣቱ ችግሮች ሲያጋጥሙ በውይይት የመፈታት ባህልን የማዳበር ልምድ ሊያካብቱ ይገባል ብለው ወጣቶች በሰላም ግንባታ ላይ የደርሻቸውን እንዲወጡ ለማሰቻል እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች እንደገለጹት መድረኩ ችግሮች ሲያጋጥሙ በውይይት የመፍታት ባህልን እንድናዳብር እና ሀገር በቀል የሠላምና የመቻቻል እሴቶችን ጠብቀን ለትውልድ ለማሻገር ከፍተኛ አስተዋፆ አለው ሲሉ ገልፀዋል።
ዜና | Oduu | News
ለቀጣይ ተልዕኮ የሚመጥን የአመራር ቁመና በመላበስ የልደታን ከፍታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ።
ጥቅምት 19, 2018
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በቀጣይ 10 ቀናት የሚተገበሩ የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ ላይ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ውይይት በማካሄድ አቅጣጫ ተቀመጠ። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ በመድረኩ ላይ እንዳሉት የህዝብንና የመንግስትን ሀላፊነት በጊዜ የለኝም መንፈስ በመስራት ከተማችን እንዲሁም ክ/ከተማው የያዙትን የልማት እና መልካም አስተዳደር ቁልፍ ተግባራት በቁርጠኝነት በማስፈፀምና በመፈፀም የተጣለብንን ሀላፊነት መወጣይ ይገባል ብለዋል። አቶ ጢቂ አያይዘው ለቀጣይ ተልዕኮ የሚመጥን የአመራር ቁመና በመላበስ የልደታን ከፍታ ለማረጋገጥ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን በትጋት፣ በቁርጠኝነት፣ በውጤት እና በስነ-ምግባር መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህ አመራር የ2018 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ከተያዙ ስትራቴጂክ ግቦች የተቀዱ የ10 ቀናት ተግባራትን መፈፀምና ማስፈፀም የሚችል የማህበረሰቡን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቁርጠኛ የሆነ፤ የሚሰጠውን ተልዕኮ አቀናጅቶ መምራትና ሀላፊነቱ በአግባቡ መወጣት የሚችል መሆን አለበት በመድረኩ አቅጣጫ ተቀምጧል። በመድረኩ ዋነኛ የትኩረት መስክ የሆኑት ሰዉ ተኮር ተግባራት፣ የፀጥታ፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የሌማት ትሩፋት እና የኢንሼቲቭ ስራዎችን ሌሎች የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ዜና | Oduu | News
በላቀ የአመራር ሰጪነት ከስኬታማ ባለሙያ ጋር ተግባራትን በቅንጅት በመስራት ተስፋ ሰጪ ለውጦች እየመጡ መሆኑ ተገለፀ
ጥቅምት 18, 2018
በመድረኩ የክ/ከተማው ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ ከክፍለ ከተማ እና ወረዳዎች ከተወጣጡ ዳሪክተሮች፣የስራ አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች ጋር በአገልግሎት አሰጣጥና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። የውይይት መድረኩን የመሩት የልደታ ክፍለ ከተማ ም/ ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አራርሳ ዲሪባ እንደገለፁት የልደታን ከፍታ ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዳሪክተሮች፣የስራ አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች የላቀ ሚና እንዳላቸው አንስተው በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚታዩ መሻሻሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በልዩ ቅንጅት እና መረባረብ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሩን ለመፍታት ለሰራተኛው ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አኳያ ስኬታማ ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ አራርሳ ድሪባ በ2018 ልደታን በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል። የውይይት መነሻ ሰነድ እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ያቀረቡት የልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጢቂ ዲሪባ እንደገለፁት በክፍለ ከተማው የአገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማነት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባው ገልፀው የውይይት መድረኩ ለስራዎች ስኬታማነት ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለፁት አስተዳደሩ ክፍለ ከተማውን ውጤታማ ለማድረግ አስተባባሪዎች እና ሰራተኞች የላቀ ሚና እንዳላቸው በማመን በቅርበት አብሮ እየተሰራበት ያለውን አግባብ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።
ዜና | Oduu | News
የክፍለ ከተማው አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት አደረገ።
መስከረም 18, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የካቢኔ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ የውሳኔ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። በውይይቱም በክፍለ ከተማው አስተዳደር ጽ/ቤቶች የቀረቡ ጥያቄዎችን እና አፋጣኝ ምላሽ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት በማካሔድ የነዋሪዎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ ውሳኔዎች ማሳለፍ ተችሏል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ለአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት የቀረቡ አጀንዳዎች የነዋሪዎችን ተጠቃሚነትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን የሚፈቱ በመሆናቸውና የአስተዳደሩን ቀጣይ ስራዎች የሚያቀላጥፉ በመሆናቸው የተቀመጠው የውሳኔ ሀሳብ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት አመላክተዋል። የካቢኔ አባላቱ ከውሳኔ ባለፈ አስተዳደሩ የጀመራቸውን የኢኒሼቲቭ ስራዎች ያሉበት ደረጃ የገመገመ ሲሆን እስካሁን የተሰሩ ተግባራት አበረታች መሆናቸው ታይቷል። በተለይ ሰው ተኮር ስራዎቹ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው እና 7/24 በሚለው መርህ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር በክ/ከተማው ቅጥር ግቢ የፅዳት ዘመቻ አካሄደ::
መስከረም 15, 2018
በእምርታ ማንሰራራት የታጀመ ህዝባዊ በዓላትን በድምቀት እናከብራለን የአካባቢያችን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል የመስቀልና ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የክ/ከተማው ሰራተኞች የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል:: በፅዳት ዘመቻው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጥቂ ድሪባ እንደገለፁት የመስቀልና የኢሬቻ በዓል ቱፊታቸውና እሴታቸውን ተጠብቆ እንዲከበር ሁሉም ሃላፊነቱን መውጣት እንዳለበት ገልፀው የመስቀልና የኢሬቻ በዓል ለማክበር የሚመጡ እንግዶቻችንን ለመቀበል አካባቢያችንን ፅዱና ውብ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል:: የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ያየህ አለም በበኩላቸው የመስቀልና የኢሬቻ በዓል የአብሮነት፣ የአንድነት፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና ህብረ - ብሔራዊ አንድነታችንና እሴቶቻችንን የሚያጎለብት መሆኑን ገልፀው በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚመጡ እንግዶቻችንን ለመቀበል በአንድነት አካባቢያችንን ንፁህና ሳቢ በማድረግ ፅዳትን ባህላችን ልናደርገው ይገባል ብለዋል:: የልደታ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀዱሽ ሓጎስ በበኩላቸው ሁሉም ማህበረሰብ አካባቢውን በማፅዳት ለመኖሪያ ምቹና ሳቢ በማድረግ ከራሳችን አልፎ እንደ ሀገር ፅዱ ከተማ የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል:: በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ ሰራተኞች በበኩላቸው ፅዳትን ባህልና የዘወትር ተግባር በማድረግ ፅዱና ውብ አካባቢ ለመፍጠር ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ::
ዜና | Oduu | News
አገልግሎት አሰጣጡን ፈጣንና የዘመነ ለማድረግ ውጤታማ የሆነ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የተቀናጀ ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ።
መስከረም 15, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ጽ/ቤት ባካሄደው የ2018 የዝግጅት ምዕራፍ ክትትልና ድጋፍና የመልካም አስተዳደርና ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤ እቅድ አቅርቦ ውይይት ተካሂዷል። በዕለቱም የክፍለ ከተማ የተቋማት ኃላፊዎች፣ የስራ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች በተገኙበት የ2018 በጀት የዝግጅት ምዕራፍ ክትትልና ድጋፍ ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል። የልደታ ክፍለ ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ ተቋማት በዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት አፈፃፀማቸውን አውቀው በተግባር ምዕራፍ ውጤታማ ለመሆን ድጋፍና ክትትሉ የጎላ ጠቀሜታ አለው በማለት ገልፀዋል። የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መመለስና ፍላጎቱን ማሟላት የሚቻለው በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ማስተካከል ይገባል ያሉት አቶ ጢቂ ድሪባ አያይዘው የሚታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል ሁሉም የራሱን ሀላፊነት መውሰድ ይገባል በማለት ገልፀዋል። አገልግሎት አሰጣጡ ለተገልጋዮች ግልጽነት ባለው አግባብ እንዲደርስ ለማስቻል በየደረጃው ከአመራር እስከ ባለሙያ ድረስ ተቀናጅተው በመስራት ቀልጣፋና ፍትሃዊ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ አቶ ጢቂ ድሪባ ገልፀዋል፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ የመልካም አስተዳደርና የቅሬታ አፈታት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ እንደገለፁት የአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ እንዲሆን የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግር በአግባብ በመፍታት የነዋሪው ጥያቄ ደረጃ በደረጃ እየፈታን መሄድ ይገባል በማለት ገልፀዋል። በመልካም አስተዳደርና ቅንጅታዊ አሰራር ላይ የተለዩ የመልካም አስተዳድር ክፍቶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ሁሉም የድርሻውን በመወጣት የያዝነውን እቅድ በማከናወን የልደታን ከፍታ ማሳየት ይገባል በማለት አቶ በላይነህ ገልፀዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም በየደረጃው ያለ አመራር፣ ቡድን መሪና ባለሙያ በተቋሙን ያለውን የስራ ባህል በማሳደግ በዝግጅት ምዕራፍ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ክፍተቶችን በማረም ውጤታማ ተግባርን በመፈፀም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በየደረጃው መፍታት እንደሚገባ ገልፀዋል።
ዜና | Oduu | News
የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ ለመገምገም በተለያዩ ወረዳዎች ምልከታ ተደረገ።
መስከረም 14, 2018
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር "በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ" ብሎ በጀመረው ፕሮግራም መሠረት የአገልግሎት አሰጣጡ ያለበትን ደረጃ ለመገምገም በተለያዩ ወረዳዎች የመስክ ምልከታ ተካሂዷል። የክ/ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ፣ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ፣ የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ በልደታ ከ/ከተማ የተለያዩ ወረዳዎች የአገልግሎት አሰጣጥ የመስክ ምልከታ አድርገዋል። በዚህም ወቅት የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ከግልፀኝነቱ ባሻገር በተለያዩ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንባ የማበስ ዕድልን እየፈጠረ መሆኑን ለምልከታ ቡድኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተገልጋዮች ተናግረዋል። ግልፀኝነትን የፈጠረው የአንድ ማዕከል አገልግሎት የብዙ ተጎጂዎችን እንባ እያበሰ፣ ችግራችን እየተፈታ ነው ሲሉ ተገልጋዮች ጨምረው ገልፀዋል። የአገልግለት ዕለትን ለተገልጋይ ብቻ በማዋል የህዝብ እሮሮን ለመቀነስ ብሎም በተገልጋዮች የሚነሱ አንገብጋቢ የሆኑ ጥያቄዎችን በአግባቡ አድምጦ ለመመለስ በሁሉም ወረዳዎች አገልግሎትን በአንድ ማዕከል መስጠት ባህል እየሆነ መምጣቱ ለመመልከት ተችሏል። በተለያዩ ምክንያቶች ለችግሮች የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በቅንነት እና በአክብሮት እያዳመጡ፣ ህግና መመሪያ በሚፈቅደው መንገድ ለሚነሱት ጥያቄዎች ደግሞ ፈጣን ምላሽ በመስጠት የተገልጋይን እሮሮ መቀነስ እየተቻለ መሆኑ አንዳንድ ወረዳዎች ገልፀዋል።
ዜና | Oduu | News
"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄዱ።
ሀምሌ 7, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤትና የወረዳ 8 አስተዳደር በጋራ አመራሮችንና የመንግስት ሰራተኞችን በማስተባበር 7ኛዉ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ችግኝ ተከላ አድርገዋል። የችግኝ ተከላውን ያስጀመሩት ያስጀመሩት የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሰፋ ቶላ ዓላማችን ዛሬ ላይ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ዛሬ የምንተክለው ነገ ለአገራችን ብሎም ለከተማችን የአየር ፀባይን ለማስተካከልና ጤናማና ለጤና ተስማሚ አየር እንዲኖረን በተለያየ አግባብ አገልግሎት ሊሰጡን የሚችሉ ችግኞችን በመትከል እንክብካቤ እና ክትትል በማድረግ ነገን በመንከባከብ ልናስቀጥል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። አረንጓዴ አሻራ የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ አጀንዳ ነው ያሉት አቶ አሰፋ ቶላ አያይዘው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ስናከናውን በላቀ ተነሳሽነት፣ ቁርጠኝነት ለሌላው አርአያነት በመሆን መትከልና በመንከባከብ እንደሚገባ ገልፀዋል ፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ እንደተናገሩት ባለሙያው አገራዊ ተልዕኮ ላይ የራሱን አሻራ ማሳረፍ መቻሉን በመግለፅ በየዓመቱ በሚደረገው የችግኝ መርሃ ግብር ላይ አላማውን በመረዳት የተቋሙ ባለሙያዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ ዛሬም አሻራቸውን በማሳረፍ እንደ አገር የተያዘውን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ሀላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪቃል እየተከናወነ በሚገኘው 7ኛው ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር ሰራተኞች በጊዶ ዋሻ በተዘጋጀው የችግኝ መትከያ ስፍራ በመትከል የዜግነት ድርሻችሁን ልትወጡ ይገባል በማለት ገልፀዋል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ገመገመ።
ሚያዚያ 28, 2018
በግምገማው ከወረዳ የተውጣጡ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለደርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን የተገልጋይና የሰራተኛ እርካታ ከማሳደግ ፣ ብቁ የሰው ሀይል ከመገንባት፣ የስልጠና ጥራትና ተደራሽነት፣ አደረጃጀትና አሰራር ማሻሻል፣ በስታንዳርድ መሰርት የሚሰጡ አገልግሎቶች ፣ የስታንዳርዳይዜሽን እና ምቹ የስራ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦዋል። የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ ህዝብና መንግስትን ከሚያስተሳስሩ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋነኛው የአገልግሎት አሰጣጥ በመሆኑ የህዝብን እርካታ ለማረጋገጥ ተቋማት በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል። በመድረኩ ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡት በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የአስተዳደር እና ፋይናንስ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ኢየሩሳሌም እንደተናገሩት ጠንካራ ተቋም የሚለየው በሚሰጠው የአገልግሎት ጥራት ላይ ተመስርቶ በመሆኑ አመራሩ ተግባራት በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ እንዲሰጡ የማድረግ ሀላፊነቱ የጎላ ነው ያሉ ሲሆን ስራዎችን እየገመገሙ መሄድ ወጥነት ያለው የአሰራር ስርአት ለመዘርጋት እንደሚያስችል ገልፀዋል። ወረዳ 6፣9 እና 10 አፈፃፀማቸውን ያቀረቡ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ተደርጎበታል።
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በወረዳዎች አስተዳደር የሚሰጡ አገልግሎቶችን አስመልክቶ ድንገተኛ ምልከታ ተደረገ።
ህዳር 24, 2018
የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ የልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ፣የመልካም አስተዳደርና ቅሬታና አቤቱታ ፅህፈት ከኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን የአገልግሎት ቀንን በማስመልከት በልደታ ወረዳ 5,3 ና 10 አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጡን ምልከታ አደረጉ፡፡ የአገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች እየታዩበት መሆኑ በምልከታው የተገለጸ ሲሆን ፡ ምልከታውን አስመልክቶ በክ/ከተማው በወረዳ 05,03 ና 10 አስተዳደር ስር የሚገኙ የስራና ክህሎት፣ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት፣ሲቪል ምዝገባና የህዝብ አገልግሎት ፥ቤቶች ጽ/ቤቶችን እና የአንድ ማዕከል አገለግሎትን እንዲሁም የስራ ቦታ ምቹነትን መሰረት ያደረገ ምልከታ ተደርጋል፡፡ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች እየታዩበት መሆኑ፥ በተለይም የአንድ ማዕከል አገለግሎት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንና እና የህጻናት ማቆያ ስፍራዎችም በተሻለ ሁኔታ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን በማውሳት ከሰራተኞች ደረት ባጅ አጠቃቀምና ስታንዳርድ ምዝገባ እንድውም የኔት ወርክ መቆራረጥ ጋር በተያያዘ ውስንነቶች መኖራቸውን የልደታ ኮሚንኬሽን ፅ/ቤት ከህዝብ አስተያየት ባአገኘው መረጃ አመልክቷል። ፈጣን ቀልጣፋና ከእጅ መንሻ የፀዳ አገልግሎት ለሁሉም ማህበረሰባችን !!!!!
ዜና | Oduu | News
በከ/ከተማው ስር የሚገኙ 10ሩወረዳዎች እና የክ/ከተማ ፅ/ቤቶች ለመመዘን የሚያስችል የምዘና አተገባበር ላይ በየደረጃው ለሚገኙ ኃላፊዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ
መጋቢት 17, 2018
በክ/ከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ የክ/ከተማ ፅ/ቤቶች እና ወረዳዎች የአፈፃፀም ምዘና ለማከናወን እንዲቻል ምዘና አተገባበር ሰነድ ላይ ለወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ ለወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ሀላፊዎች:ለፕላን እና መልካም አስተዳደር ስራ ሂደቶች አሬንቴሽን ተሰጥቷል የምዘና ትግበራ ሂደት አተገባበር ሰነድ ያቀረበ ሲሆን ምዘናው በጥምረት የሚካሄደው ሆኖ ምዘና በዋናነት በምዘና ሂደት የሚታዩ ክፍተቶችንና ቅሬታዎችን በመቀነስ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ያለውን የምዘና አፈፃፀም ወጥነት እና ተመሳሳይነት ባለው መስፈርት በተቀናጀ መልኩ ለመመዘን እዲቻል ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን ተገልፇል::የምዘና ትግበራ ሂደት፣ የመዛኝ ኮሚቴ አባላት አደረጃጀት፣ በምዘና ሂደትና ውጤት ላይ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት፣ የድረ ምዘና ስራዎች እና የአስፈፃሚ አካላት ሚና ጨምሮ መሰል ተግባራትን በዝርዝር ውይይት። በቀረበው ሰነድ ላይ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ እና አስተያየት ተሰቶባቸዋል። ከዚህም ጋር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማማት ፅ/ቤት ሀላፊ ባስተላለፉት መልዕክት ከዚህ ቀደም ሶስቱ ተቋማት የተለያየ እና ድግግሞሽ ያለው የምዘና ሂደት ያከናውኑ እንደነበር አስታውሰው ተቋማትን ወደ ተቀራረበ አፈፃፀም እንዲመጡ ለማድረግ ወጥነት ያለው የምዘና ስርዓት መዘርጋቱን ገልፀዋል። የፕላንና ልማት ሀላፊ አቶ ክብረት የምዘና ሂደቱ የተቀመጠውን መስፈርት ተከትሎ የሚከናወን በመሆኑ ስራዎችን በብቃት የሚፈፅሙትን ተቋማት ለማበረታታት እና ክፍተት የሚታይባቸውን ተቋማት ከከፍተታቸው እንዲወጡ ለማስቻለ መሆኑን ገልፀው በእውቀት ላይ የተመሰረተ ለአንድ አላማ የሚከናወን ምዘና በመሆኑ ተቋማት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በትኩረት እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።
ዜና | Oduu | News
ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር በልደታ ክ/ከተማ በመገኘት የአገልግሎት አሰጣጡን ተመለከቱ
መጋቢት 15, 2018
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ጽ/ቤቶች በመዘዋወር የአገልግሎት አሰጣጡን ቅኝት አድርገዋል። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ከዚህ በፊት የራሱ ህንፃ ባለመኖሩ ምክንያት አገልግሎቶች በተበታተነ ቦታ ሲሰጥ እንደነበረ እና በዚህም ማህበረሰቡ ጥያቄ ሲያነሳ መቆየቱ ይታወሳል አሁን ላይ ግን አስተዳደሩ የራሱን ህንፃ ገንብቶ ለአገልግሎት ምቹና ሳቢ በሆኑ ቢሮዎች የተሳለጠ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ ለክፍለ ከተማና ለወረዳ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች በመሪነት ክህሎትና በጥናትና ምርምር አሰራር ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
መጋቢት 14, 2018
የክ/ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ስልጠናውን ያዘጋጀው ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ስራ አመራር የመጡ ባለሙያዎች ደግሞ ስልጠናውን እየሰጡ ይገኛሉ ።
ዜና | Oduu | News
የ2017 በጀት አመት በግማሽ አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዝግጅትና ምዘና እንዲሁም የመካከለኛ ዘመን (2013-2017) የአራት አመት እቅድ አፈፃፀም ውይይት ተደረገበት።
ታህሳስ 21, 2018
በውይይቱም የ4 ዓመት የጽ/ቤቶች አፈፃፀምና የሪፖርት ቢጋር ለወረዳ አመራሮችና ለክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች በማቅረብ ውይይት ተደርጓል የልደታ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ እንደገለፁት ወጥ የሆነ ቢጋር በማዘጋጀትና የተቋማትን አፈፃፀሙን በጋራ በመመዘን ቀልጣፋ የሆነ አሰራር እንዲፈጠር ይረዳል በማለት በእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አዘገጃጀት የነበሩ ክፍተቶች በማረም በጥንካሬ የሚጠቀሱ ጉዳዮች በማስቀጠልና ሁሉም የተሻለ ግንዛቤ ኖሮት በትኩረት መሠራት አለበት በማለት ገልፀዋል። አቶ ጢቂ አያይዘው በወቅቱ ሪፖርት በማዘጋጀት በመገምገም ለሚመለከተው አካል በጊዜው በመላክ ጊዜውን የጠበቀ ሪፖርት እንድንሰራ የናንተ ሚና ከፍተኛ ነው በማለት ተቋሞች በቢጋሩ መሰረት ሪፖርት ማዘጋጀት በቀኑ መላክ ይኖርባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ክብረት እንደተናገሩት የተቋማት እቅዶችን በመካከለኛና በረዥም ጊዜ አድርጎ በመከፋፈል አፈፃፀማቸውን በመወያየት እንዲከለሱ በማድረግና የ5 አመት አፈፃፀም በታቀደው መሠረት እንዲፈፀም ይረዳል በማለት ሁሉም ተቋማት አፈፃፀሙን በማየትና መገምገም ቀሪ ተግባራትን አካቶ መስራት ይገባል በማለት ገልፀዋል አቶ ክብረት አክለው የጽ/ቤቶች ሪፖርት በቢጋሩ መሠረትና ጊዜውን የሚመጥንና የተቀላጠፈ እንዲሆን ተቋማት ሚናቸው ጉልህ በመሆኑ አንስተው ሶስቱ ሴክተሮችም ሪፖሪቶችን በማየትና ወጥ የሆነ ምዘና ማካሄድ ይችላሉ በማለት ገልፀዋል። ተሳታፊዎችም በተናጠል ስንሄድ ሲደረግ የነበረው የምዘና ስርዓት አሁን በጋራ ሆኖ መሠራቱ የተሻለ እና ወጥ የሆነ መሆኑ ቀልጣፋና ውጤታማ ያደርገዋል በማለት አንስተዋል።
ዜና | Oduu | News
አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የተገልጋዩን ዕርካታ ማሳደግ እንደሚቻል የልደታ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ገለጸ።
ጥር 14, 2018
ጽ/ቤቱ የመጀመሪያውን 6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ከፈጻሚ፣ከአመራርና ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል ። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ተወካይ እና የፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደር እና ፋይናንስ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ እየሩሳሌም ዮሴፍ እንደገለጹት በጽ/ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ በማቀድና ከተለያዩ ጽ/ቤቶች ጋር የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ወደ ስራ መገባቱን ገልጸው ዕቅድን መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራዎችን መስራት ተችሏል ብለዋል። ወ/ሮ እየሩሳሌም አክለውም አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ፣ የለውጥ ስራዎችን አጠናክሮ በመስራት ፣ ስነ-ምግባር ያለው ሰራተኛ በመፍጠር ፣ ተቋማትን በመደገፍ ፣የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የተገልጋዩን ዕርካታ መጨመር መቻሉን ገልፀዋል ። የጽ/ቤቱ የሰው ሀብት ልማትና ስራዎች አስተዳደር ቡድን አስተባባሪ አቶ አዲስ ደጀኔ ከክ/ከተማውና ከወረዳ ተቋማት ጋር በጋራ ትክክለኛ መረጃዎችን በመለዋወጥና የሰው ሀይልን በመጠቀም የመንግስት ሰራተኛው በአገልጋይነት መንፈስ ተገቢውን አገልግሎት መስጠትና የጽ/ቤቱን ተግባራት በስታንዳርድ በማነፃፀር ስራዎችን መስራት አለበት ብለዋል። የጽ/ቤቱ በታቀደው ልክ ስራዎችን መስራት መቻሉን ጠቁመው በቀጣይም ጽ/ቤቱ የለውጥ ስራዎችን በትኩረት በመስራትና ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት ስራዎችን ቀጣይ በትኩረት መስራት የሚገባቸው መሆኑን ገልፀዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም የቀረበው የስድስት ወር አፈፃፀም ጥሩ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም በቅንጅት ውጤታማ ስራዎችን እንሰራለን ብለዋል።
መግቢያ
ስለ_እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
ፎቶግራፎች | Photo Gallery
ቪዲዮዎች | Videos
መግለጫዎች | Press Release
መጽሄቶች | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Online TV
Web APP
የዛሬይቱ ልደታ
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ያግኙን
lidetapublic@gmail.com
+251118549979