image
image
image
image
image

የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ ለመገምገም በተለያዩ ወረዳዎች ምልከታ ተደረገ።

መስከረም 14, 2017
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር "በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ" ብሎ በጀመረው ፕሮግራም መሠረት የአገልግሎት አሰጣጡ ያለበትን ደረጃ ለመገምገም በተለያዩ ወረዳዎች የመስክ ምልከታ ተካሂዷል። የክ/ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ፣ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ፣ የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ በልደታ ከ/ከተማ የተለያዩ ወረዳዎች የአገልግሎት አሰጣጥ የመስክ ምልከታ አድርገዋል። በዚህም ወቅት የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ከግልፀኝነቱ ባሻገር በተለያዩ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንባ የማበስ ዕድልን እየፈጠረ መሆኑን ለምልከታ ቡድኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተገልጋዮች ተናግረዋል። ግልፀኝነትን የፈጠረው የአንድ ማዕከል አገልግሎት የብዙ ተጎጂዎችን እንባ እያበሰ፣ ችግራችን እየተፈታ ነው ሲሉ ተገልጋዮች ጨምረው ገልፀዋል። የአገልግለት ዕለትን ለተገልጋይ ብቻ በማዋል የህዝብ እሮሮን ለመቀነስ ብሎም በተገልጋዮች የሚነሱ አንገብጋቢ የሆኑ ጥያቄዎችን በአግባቡ አድምጦ ለመመለስ በሁሉም ወረዳዎች አገልግሎትን በአንድ ማዕከል መስጠት ባህል እየሆነ መምጣቱ ለመመልከት ተችሏል። በተለያዩ ምክንያቶች ለችግሮች የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በቅንነት እና በአክብሮት እያዳመጡ፣ ህግና መመሪያ በሚፈቅደው መንገድ ለሚነሱት ጥያቄዎች ደግሞ ፈጣን ምላሽ በመስጠት የተገልጋይን እሮሮ መቀነስ እየተቻለ መሆኑ አንዳንድ ወረዳዎች ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች