image
image
image
image
image

አገልግሎት አሰጣጡን ፈጣንና የዘመነ ለማድረግ ውጤታማ የሆነ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የተቀናጀ ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ።

መስከረም 15, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ጽ/ቤት ባካሄደው የ2018 የዝግጅት ምዕራፍ ክትትልና ድጋፍና የመልካም አስተዳደርና ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤ እቅድ አቅርቦ ውይይት ተካሂዷል። በዕለቱም የክፍለ ከተማ የተቋማት ኃላፊዎች፣ የስራ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች በተገኙበት የ2018 በጀት የዝግጅት ምዕራፍ ክትትልና ድጋፍ ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል። የልደታ ክፍለ ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ ተቋማት በዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት አፈፃፀማቸውን አውቀው በተግባር ምዕራፍ ውጤታማ ለመሆን ድጋፍና ክትትሉ የጎላ ጠቀሜታ አለው በማለት ገልፀዋል። የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መመለስና ፍላጎቱን ማሟላት የሚቻለው በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ማስተካከል ይገባል ያሉት አቶ ጢቂ ድሪባ አያይዘው የሚታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል ሁሉም የራሱን ሀላፊነት መውሰድ ይገባል በማለት ገልፀዋል። አገልግሎት አሰጣጡ ለተገልጋዮች ግልጽነት ባለው አግባብ እንዲደርስ ለማስቻል በየደረጃው ከአመራር እስከ ባለሙያ ድረስ ተቀናጅተው በመስራት ቀልጣፋና ፍትሃዊ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ አቶ ጢቂ ድሪባ ገልፀዋል፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ የመልካም አስተዳደርና የቅሬታ አፈታት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ እንደገለፁት የአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ እንዲሆን የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግር በአግባብ በመፍታት የነዋሪው ጥያቄ ደረጃ በደረጃ እየፈታን መሄድ ይገባል በማለት ገልፀዋል። በመልካም አስተዳደርና ቅንጅታዊ አሰራር ላይ የተለዩ የመልካም አስተዳድር ክፍቶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ሁሉም የድርሻውን በመወጣት የያዝነውን እቅድ በማከናወን የልደታን ከፍታ ማሳየት ይገባል በማለት አቶ በላይነህ ገልፀዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም በየደረጃው ያለ አመራር፣ ቡድን መሪና ባለሙያ በተቋሙን ያለውን የስራ ባህል በማሳደግ በዝግጅት ምዕራፍ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ክፍተቶችን በማረም ውጤታማ ተግባርን በመፈፀም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በየደረጃው መፍታት እንደሚገባ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች