image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር በክ/ከተማው ቅጥር ግቢ የፅዳት ዘመቻ አካሄደ::

መስከረም 15, 2017
በእምርታ ማንሰራራት የታጀመ ህዝባዊ በዓላትን በድምቀት እናከብራለን የአካባቢያችን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል የመስቀልና ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የክ/ከተማው ሰራተኞች የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል:: በፅዳት ዘመቻው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጥቂ ድሪባ እንደገለፁት የመስቀልና የኢሬቻ በዓል ቱፊታቸውና እሴታቸውን ተጠብቆ እንዲከበር ሁሉም ሃላፊነቱን መውጣት እንዳለበት ገልፀው የመስቀልና የኢሬቻ በዓል ለማክበር የሚመጡ እንግዶቻችንን ለመቀበል አካባቢያችንን ፅዱና ውብ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል:: የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ያየህ አለም በበኩላቸው የመስቀልና የኢሬቻ በዓል የአብሮነት፣ የአንድነት፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና ህብረ - ብሔራዊ አንድነታችንና እሴቶቻችንን የሚያጎለብት መሆኑን ገልፀው በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚመጡ እንግዶቻችንን ለመቀበል በአንድነት አካባቢያችንን ንፁህና ሳቢ በማድረግ ፅዳትን ባህላችን ልናደርገው ይገባል ብለዋል:: የልደታ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀዱሽ ሓጎስ በበኩላቸው ሁሉም ማህበረሰብ አካባቢውን በማፅዳት ለመኖሪያ ምቹና ሳቢ በማድረግ ከራሳችን አልፎ እንደ ሀገር ፅዱ ከተማ የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል:: በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ ሰራተኞች በበኩላቸው ፅዳትን ባህልና የዘወትር ተግባር በማድረግ ፅዱና ውብ አካባቢ ለመፍጠር ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ::

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች